• Why are Indigenous protocols important for all Australians? - የነባር ዜጎች ፕሮቶኮሎች ለሁሉም አውስትራሊያውያን ጠቀሜታቸው እንደምን ነው?
    Jul 4 2024
    Observing the cultural protocols of Aboriginal and Torres Strait Islander peoples is an important step towards understanding and respecting the First Australians and the land we all live on. - የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴተኛ ዜጎችን ባሕላዊ ፕሮቶኮሎች ልብ ብሎ መረዳት፤ ስለ ነባር ዜጎችና የምንኖርባት ምድር ግንዛቤ ለመጨበጥና ከበሬታን ለመቸር ጠቃሚ ወደፊት የመራመጃ እርምጃዎች ናቸው።
    Show more Show less
    9 mins
  • Indigenous art: Connection to Country and a window to the past - የነባር ዜጎች ሥነ ስዕል፤ ሀገራዊ ቁርኝትና የትናንት መስኮትነት
    Jun 27 2024
    Embracing their oral traditions, Aboriginal and Torres Strait Islander peoples have used art as a medium to pass down their cultural stories, spiritual beliefs, and essential knowledge of the land. - ቃለ ልማዶችን ሞገስ በማላበስ፤ የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ሥነ ስዕልን ባሕላዊ ወጎቻቸውን፣ መንፈሳዊ እምነቶቻቸውንና ስለ መሬታቸው ያላቸውን መሠረታዊ ዕውቀቶች የማሸጋገሪያ ተግባቦት አድርገው ተጠቅመውበታል።
    Show more Show less
    9 mins
  • Facing religious discrimination at work? These are your options - በመሥሪያ ቤትዎ የሃይማይኖት መድልዖ ገጥሞዎታል? አማራጭዎችዎን እነሆ
    Jun 19 2024
    Australia is a party to the International Covenant on Civil and Political Rights, which provides extensive protections to religious freedom. However, specific legislated protections vary across jurisdictions. If you have experienced religious discrimination at work, it is important to know your options, whether you are considering submitting a complaint or pursuing the matter in court. - አውስትራሊያ ለሃይማኖት ነፃነት መጠነ ሰፊ ጥበቃዎችን የሚቸረው የዓለም አቀፍ ሲቪልና ፖለቲካዊ መብቶች ውል ፈራሚ ናት። ይሁንና፤ የተወሰኑ ድንጋጌያዊ ጥበቃዎች እንደ ስልጣነ ግዛቱ ይለያይሉ። በመሥሪያ ቤትዎ ሃይማኖታዊ መድልዖ ደርሶብዎት ከሆነ፤ አማራጮችዎን ማወቁ ጠቃሚ ነው። ቅሬታ ማቅረብ ወይም ጉዳዩን ፍርድ ቤት ዘንድ ማቅረብ ይሹ እንደሁ።
    Show more Show less
    8 mins
  • Australia’s coffee culture explained - የአውስትራሊያ የቡና ባሕል ሲገለጥ
    Jun 7 2024
    Australians are coffee-obsessed, so much so that Melbourne is often referred to as the coffee capital of the world. Getting your coffee order right is serious business, so let’s get you ordering coffee like a connoisseur. - አውስትራሊያውያን አቅላቸው ለቡና የማለለ ነው፤ ተዘውትሮም ሜልበርን የዓለም የቡና መዲና በሚል ተቀጥላ ትጠቀሳለች። ቡናዎን በውል ማዘዝም ሁነኛ ጉዳይ ነው፤ ልክ ቡናን በማጣጣም ክህሎት እንደተላበሰ ባለሙያ ቡናዎን እንዘዝልዎት።
    Show more Show less
    8 mins
  • Should you consider private health insurance? - የግል የጤና ኢንሹራንስ ለመግባት ይሻሉን?
    May 28 2024
    Australians have access to a quality and affordable public healthcare system. There's also the option to pay for private health insurance, allowing shorter waiting times and more choices when visiting hospitals and specialists. - አውስትራሊያውያን ጥራትና ለአቅም መጣኝ የሆነ የሕዝብ ጤና ክብካቤ ሥርዓት አላቸው። እንዲሁም፤ ሆስፒታሎችንና ስፔሻሊስቶችን ሲጎበኙ አጭር የቆይታ ጊዜን የሚያመቻችልዎና ተጨማሪ ምርጫዎች የሚፈቅድልዎ አማራጭ የግል የጤና ኢንሹራንስም አለ።
    Show more Show less
    9 mins
  • What were the Australian Wars and why is history not acknowledged? - የአውስትራሊያ ጦርነቶች ምን ነበሩ፤ ታሪክ ዕውቅና ያልቸራቸው ስለምን ነው?
    May 24 2024
    The Frontier Wars is a term often used to describe the more than 100 years of violent conflicts between colonial settlers and the Indigenous peoples that occurred during the British settlement of Australia. Even though Australia honours its involvement in wars fought overseas, it is yet to acknowledge the struggle that made it the country it is today. - የሠፋሪና ነባር ዜጎች ጦርነቶች ቃሉ በእንግሊዝ የአውስትራሊያ ሠፈራ ወቅት ከ100 ዓመታት በላይ በቅኝ ገዢ ሠፋሪዎችና በነባር ዜጎች መካከል የተካሔዱ ግጭቶችን ለመግለጥ ተዘውትሮ ይነገራል። ምንም እንኳ አውስትራሊያ የተሳተፈችባቸውን የባሕር ማዶ ጦርነቶች ክብር ብትቸርም፤ አሁን ያለችውን ሀገር ለፈጠረው ትግል ግና እስካሁን ዕውቅናን አልቸረችም።
    Show more Show less
    13 mins
  • Understanding the profound connections First Nations have with the land - ነባር ዜጎች ከመሬታቸው ጋር ያላቸውን ጥልቅ ቁርኝቶች መረዳት
    May 2 2024
    The land holds a profound spiritual significance for Aboriginal and Torres Strait Islander peoples, intricately intertwined with their identity, belonging, and way of life. - ለአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች መሬት ጥልቅ መንፈሳዊ ፋይዳን የያዘ፣ ከማንነታቸው፣ ውሁድነትና የአኗኗር ዘዬ ጋር ተጋምዶ የተቆራኘ ነው።
    Show more Show less
    7 mins
  • Tackling misinformation: How to identify and combat false news - ሐሰተኛ መረጃን መገደብ፤ ሐሰተኛ ዜናዎችን እንደምን መለየትና መፋለም እንደሚቻል
    Apr 23 2024
    In an era where information travels at the speed of light, it has become increasingly difficult to distinguish between true and false. Whether deemed false news, misinformation, or disinformation, the consequences are the same - a distortion of reality that can affect people's opinions, beliefs, and even important decisions. - መረጃ በብርሃን ፍጥነት በሚጓዝበት ዘመን፤ እውነትና ሐሰቱን ለመለየት አዋኪነቱ እየጨመረ መጥቷል። ሐሰተኛ ዜናዎች፣ ሐሰተኛ መረጃም ይሁን ወይም አሳሳች መረጃ ይባሉ መዘዞቻቸው ተመሳሳይ ነው፤ የሰዎችን አተያዮችና አመኔታዎች በማዛባት ሲልም ጠቃሚ ውሳኔዎች ላይ ተፅዕኖን ያሳድራሉ።
    Show more Show less
    13 mins