• የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ

  • De: SBS
  • Podcast

የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ  Por  arte de portada

የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ

De: SBS
  • Resumen

  • ይህ ፕሮጄክት ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የትውልድ አገራቸውን ስለምን ለቅቀው እንደወጡ፣ በተለያዩ አገራት የስደት ሕይወት ውስጥ እንደምን እንዳለፉና በታደገቻቸው ሁለተኛ አገራቸው አውስትራሊያ የዳግም ሠፈራ ሕይወት የገጠሟቸውን ተግዳሮችና የተቸሯቸውን መልካም ዕድሎች ለማንፀባረቅ ያለመ ነው። ትረካዎቹ የኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የግለሰብ ሕይወት ጉዞዎች፣ ስኬቶች፣ ትግሎች፣ አይበገሬነትና ለአውስትራሊያ መብለ-ባሕል ድርና ማግ ያበረከቷቸውን ማለፊያ አስተዋፅዖዎች አጉልቶ ለማሳየት ነው።
    Copyright 2024, Special Broadcasting Services
    Más Menos
activate_primeday_promo_in_buybox_DT
Episodios
  • የስደተኞች ሳምንት 2024፤ ድምፃዊ ኤልያስ የማነ "ኪዊ" - ከአፍሪካ ቀንድ እስከ እስያ ፓስፊክ
    Jun 21 2024
    የዓለም የስደተኞች ቀን ከ2001 አንስቶ ወርሃ ጁን በገባ በ20ኛው ቀን ሲከበር፤ አውስትራሊያ ውስጥ ጁን 20ን አካትቶ ከአንድ ቀን መታሰቢያነት ዝለግ ብሎ ከጁን 16 እስከ 22 አንድ ሳምንት ደፍኖ ይከበራል። ይህንኑ አስባብ አድርገን ከሶማሊያ ተንስቶ፣ በኬንያና ኒውዝላንድ አቋርጦ አውስትራሊያ የሠፈረውን ድምፃዊ ኤልያስ የማነ "ኪዊ" ከቀደም የግለ ታሪክ ወጉ ቀንጭበን አቅርበናል።
    Más Menos
    19 m
  • "የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግፎ እዚህ አድርሶኛል፤ ከአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ የምሻው 'አይዞህ' የሚል የሞራል ድጋፍ ነው" ለማ ክብረት
    Jun 2 2024
    በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅት የቀድሞው ዝነኛ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በረኛ ለማ ክብረት፤ ከውልደት እስከ ዕድገት፣ ከቁስቋም የሶስተኛ ክፍል እግር ኳስ ተጫዋችነት እስከ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂነት እንደምን እንደ ደረሰ አውግቷል። በቀጣዩ ትረካው ከሞሪሽየስ ጥገኝነት ጥየቃ እስከ አውስትራሊያ ዳግም ሠፈራ ያለ የሕይወት ጉዞውን ነቅሶ ያወጋል።
    Más Menos
    14 m
  • ለማ ክብረት፤ ከቁስቋም እስከ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በረኛነት
    Jun 2 2024
    ለማ ክብረት፤ በቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ባልደረባው ኤርሚያስ ወንድሙ አንደበት "ምናልባትም ከዓለም ምርጥ በረኛ" የተሰኘ፤ ሞሪሽየስ ላይ ከአምስት የመለያ ፍፁም ቅጣት ምቶች አራቱን በማዳን የሀገሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለድል ያበቃ ስመ ጥር ግብ ጠባቂ ነው።
    Más Menos
    15 m

Lo que los oyentes dicen sobre የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ

Calificaciones medias de los clientes

Reseñas - Selecciona las pestañas a continuación para cambiar el origen de las reseñas.