Episodios

  • የስደተኞች ሳምንት 2024፤ ድምፃዊ ኤልያስ የማነ "ኪዊ" - ከአፍሪካ ቀንድ እስከ እስያ ፓስፊክ
    Jun 21 2024
    የዓለም የስደተኞች ቀን ከ2001 አንስቶ ወርሃ ጁን በገባ በ20ኛው ቀን ሲከበር፤ አውስትራሊያ ውስጥ ጁን 20ን አካትቶ ከአንድ ቀን መታሰቢያነት ዝለግ ብሎ ከጁን 16 እስከ 22 አንድ ሳምንት ደፍኖ ይከበራል። ይህንኑ አስባብ አድርገን ከሶማሊያ ተንስቶ፣ በኬንያና ኒውዝላንድ አቋርጦ አውስትራሊያ የሠፈረውን ድምፃዊ ኤልያስ የማነ "ኪዊ" ከቀደም የግለ ታሪክ ወጉ ቀንጭበን አቅርበናል።
    Más Menos
    19 m
  • "የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግፎ እዚህ አድርሶኛል፤ ከአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ የምሻው 'አይዞህ' የሚል የሞራል ድጋፍ ነው" ለማ ክብረት
    Jun 2 2024
    በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅት የቀድሞው ዝነኛ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በረኛ ለማ ክብረት፤ ከውልደት እስከ ዕድገት፣ ከቁስቋም የሶስተኛ ክፍል እግር ኳስ ተጫዋችነት እስከ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂነት እንደምን እንደ ደረሰ አውግቷል። በቀጣዩ ትረካው ከሞሪሽየስ ጥገኝነት ጥየቃ እስከ አውስትራሊያ ዳግም ሠፈራ ያለ የሕይወት ጉዞውን ነቅሶ ያወጋል።
    Más Menos
    14 m
  • ለማ ክብረት፤ ከቁስቋም እስከ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በረኛነት
    Jun 2 2024
    ለማ ክብረት፤ በቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ባልደረባው ኤርሚያስ ወንድሙ አንደበት "ምናልባትም ከዓለም ምርጥ በረኛ" የተሰኘ፤ ሞሪሽየስ ላይ ከአምስት የመለያ ፍፁም ቅጣት ምቶች አራቱን በማዳን የሀገሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለድል ያበቃ ስመ ጥር ግብ ጠባቂ ነው።
    Más Menos
    15 m
  • "በእኔ በኩል ቀጣዩ ሕይወቴ አውስትራሊያ ይሁን ኢትዮጵያ አላውቅም" ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ
    May 26 2024
    በአንድ የጀርመን ባለስልጣን "ሰርከስ ኢትዮጵያ ጀርመን ውስጥ ኮካ ኮላ የሚታወቀውን ያህል በልጆች ዘንድ ይታወቃል" የተባለለት ድርጅት ዳይሬክተር የነበረው ዐቢይ አየለ፤ ስለ ጥገኝነት ጥየቃ ውጣ ውረዶችና የአውስትራሊያ ሕይወት ጉዞ ጅማሮው ይናገራል።
    Más Menos
    18 m
  • "ከ30 የሰርከስ ኢትዮጵያ አባላት ውስጥ 15ታችን አውስትራሊያ ጥገኝነት ጠይቀን ቀረን" ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ
    May 26 2024
    የቲአትርና ፊልም ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ፤ በቀዳሚ ክፍለ ዝግጅታችን ስለ ትውልድና ዕድገቱ፣ የቀለም ትምህርትና የጥበብ ዕውቀት ቀሰማውን ከሰርከስ ኢትዮጵያ መቀላቀሉ ጋር አሰናስሎ አንስቷል። በሀገረ አውስትራሊያ የጥገኝነት ጥየቃው ውሳኔውን አስከትሎ ያወጋል።
    Más Menos
    14 m
  • ዐቢይ አየለ፤ ከአዋሬ እስከ አውስትራሊያ
    May 21 2024
    የቲአትርና ፊልም ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ፤ ከጥበብ ሙያ ጅማሮው ተነስቶ፤ የስደት ጉዞውን አጣቅሶ እስከ አውስትራሊያ የሠፈራ ሕይወቱ ያወጋል።
    Más Menos
    14 m
  • መለስ ሳህሌ፤ ከድሬዳዋ እስከ አውስትራሊያ
    May 14 2024
    የቀድሞው የSBS አማርኛ አገልግሎት ዋና አዘጋጅ መለስ ሳህሌ፤ ስለ ድሬዳዋ ትውልድና ዕድገቱ፣ የጂቡቲ ስደት ፈተናዎቹና የአውስትራሊያ የሠፈራ ሕይወቱ ያወጋል።
    Más Menos
    12 m
  • ዶ/ር ብሩክ ይርሳው፤ ከድሬዳዋ እስከ አውስትራሊያ
    Feb 6 2024
    ዶ/ር ብሩክ ይርሳው፤ እንደምን ከአገረ ኢትዮጵያ በጃፓን ዞረው ለአውስትራሊያ ምድር እንደበቁ፤ የትምህርት፣ የሥራ፣ የቤተሰብ፣ ማኅበረሰባዊና መንፈሳዊ ሕይወት ትስስሮሻቸውን አንስተው ያወጋሉ።
    Más Menos
    14 m