Episodios

  • DW Amharic የነሐሴ 9 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    Aug 15 2024
    የጋምቤላ ምክር ቤት ዓለሚቱ ኡሞድን በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የክልል ፕሬዝደንት አድርጎ ሾመ። ከኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር 32 የጭነት ሎኮሞቲቮች 17ቱ አይሰሩም ተባለ። በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ የግብረ-ሠናይ ሠራተኛ ማንነቱ ባልታወቀ ወንጀለኛ ቡድን ተገደሉ። የ15 ዓመቱ ሔመን በቀለ የታይም መጽሔት የዓመቱ ምርጥ ታዳጊ ተብሎ ተመረጠ። የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት የአድሬ የድንበር መሸጋገሪያን ለሦስት ወራት ሊከፍት ነው። በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጦጣ ፈንጣጣ 548 ሰዎች መግደሉ ተገለጸ። በጋዛ ተኩስ ለማስቆም የታቀደው የዶሐ ድርድር ያለ ሐማስ ተሳትፎ ተጀመረ።
    Más Menos
    9 m
  • DW Amharic የነሐሴ 8 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    Aug 14 2024
    ሶማሌላንድ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን የምታሸማግለው ቱርክ ገለልተኛ አይደለችም ስትል ከሰሰች። የሶማሌላንድ ክስ የተደመጠው በአንካራ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሔደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ውይይት ያለ ውጤት ከተበተነ በኋላ ነው። የሱዳንን ጦርነት ለማብቃት ያለመ ድርድር የብሔራዊው ጦር አዛዥ ጄነራል አብደል ፋታኅ አል-ቡርኻን በሌሉበት ተጀመረ። ግብጽ እና ሶማሊያ የወታደራዊ ትብብር ፕሮቶኮል ሥምምነት ተፈራረሙ። በጋዛ ውጊያ የገጠሙ ኃይሎች ተኩስ እንዲያቆሙ ለማድረግ ያቀደ ድርድር በቃጣር ሊካሔድ ነው። ጀርመን የኖርድ ስትሪም የጋዝ ማስተላለፊያን በማፈንዳት የጠረጠረችውን ግለሰብ ለመያዝ የእስር ማዘዣ አወጣች።
    Más Menos
    9 m
  • የነሐሴ 7 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    11 m
  • የነሐሴ 6 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    Aug 12 2024
    የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት የህወሓት “የሕግ ሰውነት፤ አግባብ ባለው ሕግ እና በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሠራር መሠረት ብቻ እልባት ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ” እንደሆነ አስታወቀ። የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሀገሮቻቸው መካከል የተቀሰቀሰውን ውጥረት ለማብቃት በቱርክ አሸማጋይነት በአንካራ ተገናኙ። በዩጋንዳ በደረሰ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 23 ደረሰ። በጋዛ በአስቸኳይ ተኩስ እንዲቆም ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ዩናይትድ ኪንግደም ጥሪ አቀረቡ። ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ወደ ሩሲያ ግዛት የገቡ የዩክሬን ወታደሮችን የሀገራቸው ጦር እንዲያባርር ትዕዛዝ ሰጡ
    Más Menos
    10 m
  • የሐምሌ 5 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    11 m
  • የነሐሴ 4 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    10 m
  • የአርብ ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
    Aug 9 2024
    በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ግንደወይን ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ ወንዝ ውስጥ የሰጠሙ ሰዎች አስከሬን የማፈላለግ ስራ መቀጠሉ ተገለፀ። አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ህወሓት አካሂዳለሁ ካለው ጠቅላላ ድርጅታዊ ጉባኤ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ። ሊባኖስ ውስጥ ያለው ሁኔታ የሚባባስ ከሆነ በተለይ ችግር ያለበት አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለማውጣት ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሾፍቱ ከተማ አከባቢ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሊያስገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የሱዳን መንግሥት ከአሜሪካ ጋር ለመመካከር የልዑካን ቡድኑን ወደ ጅዳ እንደሚልክ ገለፀ።
    Más Menos
    10 m
  • DW Amharic የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 2 ቀን 2016 ዓ.ም.ሃሙስ
    Aug 8 2024
    --የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን “የፕሬዚዳንቱ የሕይወት ዘመን ሽልማት” ተበረከተለት፡፡ --በኢትዮጵያዋ ሶማሌ ክልል በዋቢ ሸቤሌ ወንዝ እስከ ገደፉ ሞልቶ በተከሰተ ጎርፍ ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ከመኖርያ ቀዬያቸው መፈናቀላቸውን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። --የተለያዩ የኤርትራ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሥልጣን ላይ ያለውን አምባገነን ያሉትን መንግሥት ለመታገል የጋራ ጥምረት መመስረታቸውን አስታወቁ። --ኬንያ የወጣቶች ተቃውሞ ዛሬ በመዲናዋ ናይሮቢ በርካታ ወጣቶች በተሳተፉበት ዳግም መቀስቀሱ ተነገረ።
    Más Menos
    12 m